Divine Liturgy Service Hours: Saturday @ 5:00 am – 8:00 am | Sunday @ 4:00 am – 7:00 am

፩. መግቢያስያሜና ምንነት
ምኩራብ ማለት በቀጥታ ትርጉሙ “መሰብሰቢያ” ወይም “መማሪያ” ማለት ነው። ቅዱስ ያሬድ የጌታን ጾም ሳምንታት በሰየመበት ስያሜው ሦስተኛውን ሳምንት ጌታ በምኩራብ ማስተማሩን፤ መስበኩንና መፈወሱን ለማስታወስ ምኩራብ ብሎ ሰይሞታል። የምኩራብ ሥርዓት የተጀመረው በባቢሎን ነው። እስራኤላውያን በናቡከደነጾር ተማርከው ወደ ባቢሎን ሲሄዱ፣ የነበረው አንድ መቅደስ (የሰሎሞን መቅደስ) ፈርሶ ነበር። በኦሪት ሕግ መሠረት ደግሞ በባዕድ ሀገር መቅደስ መሥራት አይፈቀድም ነበር (መሥዋዕት የሚሰዋው በኢየሩሳሌም ብቻ ስለነበር)።

ይህም አገልግሎት እስራኤላውያን ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ በኋላም የቀጠለ ሲሆን በተለያዩ ሥፍራዎች ተስፋፍቶ በየሰንበቱም ብዙ ሕዝብ ወደ ምኩራቦች ይሰበሰብ ነበር። (ሐዋ 9፥2 ፤ 13፥3)

፪. የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምኩራብ አገልግሎት

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ ወደእነዚህ ምኩራቦች በተደጋጋሚ በመገኘት አስተምሯል፤ የመንግስትንም ወንጌል ሰብኳል፤ በሕዝብም ዘንድ እየተመላለሰ የሥጋ ደዌንና ሕማምን በተዓምራት ፈውሷል፡፡ (ማቴ.4÷23፤ ማር.1÷39)፡፡ በአንድ ምኩራብ የሚሰባሰቡት ሰዎች ጥቂት ሰዎች ስለሆኑ ለማስተማር ቀላልና የእያንዳንዱን አማኝ ሐሳብና ራዕይ ለማወቅም የሚያስችል ነው። ጌታ በአንድ ምኩራብ በተደጋጋሚና ባለመሰልቸት ከመቅደስ ይልቅ እየተገኘ ማስተማሩን ወንጌል እንዲህ ይመሰክርልናል እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገባ፥ ሊያነብም ተነሣ።”(ሉቃ.4÷16)

አምላካችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደእነዚህ ምኩራቦች እየገባ ያስተማረበትንም ምክንያት እንደሚከተለው መመልከት ይቻላል፦

 ሐዋርያትም እንደጌታ ልማድ እንዲሁ በመቅደስ እየተገኙ በተደጋጋሚ አስተምረዋል፡፡ “በስልማናምበነበሩጊዜ በአይሁድ ምኵራቦች የእግዚአብሔርን ቃል ሰበኩ”(ሐዋ.13÷5)፡፡“ በአንፊጶልና በአጶሎንያም ካለፉ በኋላ ወደ ተሰሎንቄ መጡ፥በዚያም የአይሁድ ምኵራብ ነበረ። ጳውሎስም እንደ ልማዱ ወደ እነርሱ ገባ፥ሦስት ሰንበትም ያህል ከእነርሱ ጋር ከመጻሕፍት እየጠቀሰ ይነጋገር ነበር…”(ሐዋ.17÷1-2)፡፡

ይህ ሳምንት ለዛሬዋ ቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው ትልቅ ትምህርት “አገልግሎት” በመቅደስ ቅጥር ብቻ መወሰን እንደሌለበት ነው። የምኩራብ አገልግሎት ለአማኙ የግል ሕይወትና ችግር ቅርብ የሆነ የአገልግሎት ዓይነት ነው። ዛሬም ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ወደ መቅደሱ እስኪመጡ ብቻ ከመጠበቅ ይልቅ፣ ልክ እንደ ጌታችንና እንደ ሐዋርያት ሁሉ ወደ ሕዝቡ መንደርና ቤት በመውረድ የሰዎችን ችግር የሚረዳና የሚያጽናና አገልግሎት መስጠት ይገባታል። ይህም አማኙን ከውጫዊ ሥርዓት ባለፈ በቃለ እግዚአብሔር ታንጾ ለሥጋ ወደሙ እንዲበቃና እውነተኛ ክርስቲያናዊ ሕይወት እንዲመራ ይረዳዋል።

  1. የዕለቱ ምንባባትና መዝሙር ምስጢር
  2. ዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)

ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት አነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምስያጥ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ ቦአ ምኩራቦሙ ወገሠፆሙ ያርምሙ አንከሩ ምህሮቶ ሞገስ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ፡፡

ትርጉም:- ጌታችን ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ፤ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ፤ ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም የሰንበት ጌታዋ ነው ፡፡ያባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት፤ቤቴስ የጸሎት ቤት ይባላል (እያለ የሃይማኖትን ቃል አስተማራቸው፡)፡ ወደ ምኩራባቸውም ገብቶ ዝም ይሉ ዘንድ ገሠፃቸው፤ እነርሱም ትምህርቱን፣ የቃሉን ግርማ፣ የአነጋገሩን ጣዕምና፣ የአንደበቱን ቅልጥፍና አደነቁ።

፫. ምንባባት

ቤተ ክርስቲያን በዚህ ሳምንት የምታነባቸው ክፍሎች ሁሉም አንድ መልእክት አላቸው፦

፬. ማጠቃለያ

ምኩራብ የዓቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት ሲሆን፣ ጌታችን በምኩራብ ገብቶ ያስተማረውንና የፈወሰውን ተግባር ለማሰብ በቅዱስ ያሬድ የተሰየመ ነው። ምኩራብ የተጀመረው አይሁድ በባቢሎን ምርኮ ሳሉ የኢየሩሳሌም መቅደስ በመፍረሱ ምክንያት፣ በየሰፈራቸው ተሰብስበው ለመማርና ለመጸለይ በሠሩት አነስተኛ ቦታ ነው። ጌታችንም ወደ ሕዝቡ ለመቅረብና የእያንዳንዱን ችግር ለመረዳት ሲል በየምኩራቡ ገብቶ ማስተማርን ልማድ አድርጎት ነበር። ይህ ሳምንት ለዛሬዋ ቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው ትልቅ መልእክት፣ አገልግሎት በመቅደስ ብቻ መወሰን እንደሌለበትና አገልጋዮች አማኙ ባለበት አድራሻ ሄደው ማስተማርና መርዳት እንዳለባቸው ነው። በዕለቱ የሚነበቡት የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍሎችም እምነት ያለ መልካም ሥራ ትርጉም እንደሌለውና የእግዚአብሔር ቤት ለንግድ ሳይሆን ለጸሎትና ለምሕረት ብቻ መዋል እንዳለበት ያስገነዝቡናል።ባጭሩ “ምኩራብ” ማለት፦

  1. እግዚአብሔርን በየቦታውና በየሰፈሩ መፈለግ፣
  2. ቃሉን በጥልቀት ማጥናትና መረዳት፣
  3. አገልጋይ ወደ ሕዝቡ ቤትና ሕይወት ዝቅ ብሎ መውረድ፣
  4. እምነትን በምሕረትና በቸርነት ሥራ መግለጥ ማለት ነው።

በዚህ በተቀደሰው ሳምንት፣ በትጋት ጾመንና ጸልየን፣ ከኃጢአት ርቀንና በንስሐ ታድሰን የቅድስናን ሕይወት ገንዘብ ልናደርግ ይገባል። አምላካችን እግዚአብሔር በዚህ ሳምንት በረከቱን ያድለን፤ በቸርነቱ ተቀድሰን ለትንሣኤው ብርሃን እንዲያበቃን የዘወትር ጸሎታችን ይሁን።

የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና የቅዱሳን በረከት አይለየን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

ይቆየን!

ምንጭ፡ https://eotcmk.org/a/ምኩራብ-2/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *