Divine Liturgy Service Hours: Saturday @ 5:00 am – 8:00 am | Sunday @ 4:00 am – 7:00 am

የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት “መጻጉዕ”

አራተኛ ሳምንት - መጻጉዕ

የስሙትርጉም «መጻጒዕ» የሚለው ቃል የግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «በሽተኛ» ወይም «ድውይ» ማለት ነው ። በዚህም ሳምንት ጌታችን በመዋዕለ ሥጋዌው (በምድር በነበረበት ወቅት) ካደረጋቸው ታላላቅ ተአምራት መካከል አንዱ የሆነውንና ለ፴፰ (ሠላሳ ስምንት) ዓመታት ያህል በአልጋ ቁራኝነት ተይዞ የነበረውን በሽተኛ የፈወሰበትን ድንቅ ተአምር እናስባለን ።ቅዱስ ያሬድም በደዌ የተያዙ ወገኖች ሁሉን ቻይ የሆነውን ጌታ ተስፋ ያደርጉ ዘንድና በክርስቶስ […]

የዐቢይ ጾም ሶስተኛ ሳምንት “ምኩራብ”

Mikurab

፩. መግቢያ፡ስያሜና ምንነትምኩራብ ማለት በቀጥታ ትርጉሙ “መሰብሰቢያ” ወይም “መማሪያ” ማለት ነው። ቅዱስ ያሬድ የጌታን ጾም ሳምንታት በሰየመበት ስያሜው ሦስተኛውን ሳምንት ጌታ በምኩራብ ማስተማሩን፤ መስበኩንና መፈወሱን ለማስታወስ ምኩራብ ብሎ ሰይሞታል። የምኩራብ ሥርዓት የተጀመረው በባቢሎን ነው። እስራኤላውያን በናቡከደነጾር ተማርከው ወደ ባቢሎን ሲሄዱ፣ የነበረው አንድ መቅደስ (የሰሎሞን መቅደስ) ፈርሶ ነበር። በኦሪት ሕግ መሠረት ደግሞ በባዕድ ሀገር መቅደስ መሥራት አይፈቀድም […]

የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት “ዘወረደ”

መግቢያ ዐቢይ ጾም የአጽዋማት ሁሉ የበላይ ወይም “ጉልላት” ተብሎ ይጠራል። ይህ ጾም “እጸድቅ አይል ጻድቅ፣ እነጻ አይል ንጹሐ ባሕርይ” የሆነው አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውን ለማዳን ሰው ከሆነ በኋላ፣ በየጥቂቱ አድጎ የአገልግሎቱ ሁሉ መጀመሪያ፣ የጥምቀቱ ማግስት አድርጎ ለእኛ ለልጆቹ አርአያነትን ያሳየበት ነው። ጌታችን “ከእኔ ተማሩ” (ማቴ. 11:29) እንዳለ፣ ፈለጉን በመከተል ይህንን ታላቅ ጾም እንጾማለን። በዐቢይ […]