Divine Liturgy Service Hours: Saturday @ 5:00 am – 8:00 am | Sunday @ 4:00 am – 7:00 am

ቤተ አርድዕት

እንኳን ደና ወደ ቤተ አርድዕት መጡ

መች ተመሠረተ ፡ መስከረም 29፣ 2016 ዓ.ም

በምን መልኩ ደብሩን ያገለግላል

  • ከደብሩ አገልግሎት በተጨማሪ እንደዋነኛ ሆኖ መታየት የሚገባው ቤቱ የተመሠረተው በዚሁ ደብርና አካባቢው እንዲሁም አልፎም ዓለም ላይ የሚገኙ በዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ወጣት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እግዚአብሔርን ለማሳወቅ ነው። ትምህርቶችን በመስጠት፣ የእግዚአብሔርን አባትነትና ፍቅር በማስረጽ እርሱን የፈለጉ ሁሉ በምሥጢራት ሕይወት እንዲካፈሉ፣ አላፊ ከሆነች ዓለም ራሳቸውን ጠብቀው አምላክን በማመስገን በቤቱ እንዲጸኑ ማድረግ ተቀዳሚ ተግባሩ ነው።
  • በደብሩ ባሉ የተለያዩ ክፍላት በመሳተፍ የደብሩን አገልግሎት ለማስፋት ይሠራል። በዋናነት ከሚጠቀሱት መካከል፡
    • ክህነታዊ አገልግሎት፡ በዚህ ቤት ውስጥ ከ20 ያላነሱ አገልጋይ ዲያቆናት ያሉ ሲሆን (ከ15 በላይ የምሆኑት የክህነት ሽልማቱን ያገኙት በዚሁ ሀገር እንደሆነ ሳይዘነጋ) በቅዳሴ፣ በማኅሌት፣ ልጆችን በማስተማር እና መሰል ክህነትን በሚጠይቁ አገልግሎቶች ላይ ይሳተፋሉ።
    • ትምህርት ክፍል፡ የወንጌልን ተደራሽነት ለማስፋት በደብሩ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ክፍላት እንዲሁም በአካል መገኘት ላልቻሉ ደግሞ በተለያዩ የበይነ መረብ መስኮቶች ወንጌልን በስብከትና በኮርስ መልክ የሚያደርሱ አባላትን በውስጡ ይዟል።
    • ሚዲያ ክፍል፡ ሌላው ዋነኛ የአገልግሎት መድረክ ሲሆን በዚህ ቤት የሚገኙ በርከት ያሉ አባላትም የደብሩን የሚዲያ እንቅስቃሴ በተለያዩ ሙያዊ ተግባራት ያግዛሉ።
    • እንዲሁም አምላክ በሰጣቸው ልዩ ልዩ ሥጦታዎች እርሱ እንደፈቀደ መጠን ደብሩ በሚያካሂዳቸው ሌሎች አገልግሎቶችም ለመሰለፍ የበረቱ አባላትን ይዟል።

በሳምንት ውስጥ ያላችሁ መርሃግብሮች ምንድን ናቸው (ከነ ሰአታቸው)

  • ቤተ አርድዕት የተመሠረተው በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (universities) ውስጥ ባሉ ተማሪዎች በመሆኑ እያንዳንዱ የራሱ የሆነ መርሐግብር ይኖረዋል። ሁሉንም በአንድ የሚያገናኘው ግን የሚከተለው ነው
    • ቅዳሜ ከቅዳሴ በኋላ ከ8:30 am እስከ 10:30 am- ሁሉንም ያካተተ ጉባኤ ይደረጋል። በዚህም ትምህርቶች፣ መዝሙራት፣ ልዩ ልዩ መወያያዎች እንዲሁም ኪነ ጥበባዊ ሥራዎች ይቀርባሉ።

የክፍሉ ተልእኮ (Mission) :

  • በልዩ ልዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎችን ወደ እግዚአብሔር ቤት በወንጌል ቃልና በተግባር በመሳብ የአባትነት ፍቅሩን በማሳየት የእርሱ ታማኝ አገልጋዮች ማድረግ!

ራእይ (Vision)፡

  • በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎትን የተማሩ፣ በጎ ምግባርና ቀና ሃይማኖትን የተላበሱ አገልጋዮችን ነገ ቤተ ክርስቲያን በምትፈልጋቸው የትኞቹም የአገልግሎት መድረኮች ላይ እንዲሳተፉ እና ለምእመናን አልፎም ለሀገርና ለዓለም ይህች ውብ የሆነችውን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዲያስተዋውቁ ማድረግ።

እሴት (Value)፡

እሴት (Value)ማብራሪያ
ትጋት በክህነትና በትምህርትየእግዚአብሔርን ቃልና ምሥጢራት ለመማርና በተማሩት ለማገልገል ሁልጊዜ ቁርጠኛ መሆን።
ታማኝነትና ንጽሕናበምሥጢራት ሕይወት ጸንቶ በመኖር፣ ከአላፊ ዓለም ራስን ጠብቆ፣ የክርስቶስን አባትነትና ፍቅር በማንገብ ታማኝ አገልጋዮች መሆን።
የወንጌል ተደራሽነትወንጌልን በስብከትና በኮርስ እንዲሁም በተለያዩ የበይነ መረብ መስኮቶች ተደራሽ በማድረግ
እግዚአብሔርን ለዓለም ማስተዋወቅ።
አገልግሎትን ማስፋትበደብሩ ባሉ የተለያዩ ክፍሎች በመሳተፍና በመተባበር የደብሩን አገልግሎት ለማስፋት
መሥራት።

Meeting Times

N/A

 

 

 

 

 

schedule

N/A