Divine Liturgy Service Hours: Saturday @ 5:00 am – 8:00 am | Sunday @ 4:00 am – 7:00 am

ሃይማኖት ማለት ምን ማለት ነው?

ሃይማኖት መዝገበ ቃላዊ ፍቺ፡- አንደ አለቃ ኪዳነ ወል ክፍሌ የአማረኛ መዜገበ ቃላት ትርጓሜ ማመን፤ መታመን፤
እመነት፤ ጽኑ ተስፋ ፤የአምልኮት ባሕል ማለት ነው ብለው ይተረጉሙታል፡፡
የደስታ ተክለወልድ ደግሞ ሃይመነተ(አመነ) ካለው ግስ የተገኘ ስሆን ትርጓሜውም አሚን ፤ማመን፤ እምንት፤ ማለት ነው
ብለውታል፡፡

ከላይ ያለውን ትርጓሜ ሁለት መሠረታዊ ነጥቦችማንሳት ይቻላል፡፡ አንደኛ ሓይማት ማለት በዓይን የማይታየውን በእጅ
የማይዳሰሰውን በአጠቃላይ ከሰው አዕምሮ እውቀት እና ኅሊና ምርምር በላይ የሖነውን በስሜት ሕዋሳት ማረጋገጥ
የማይቻለውን ማመን/መቀበል የሚልን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሃይማኖት ከሚለው ቃል መታመን የሚልን ትርጓሜ
ካገኘን ይህን ቃል በሌላ አባባል ብንለው ሃይማተኛ/ታማኝ ማትን ነው፡፡ በሌላ አባባል ሲያምኑ የአምላክን መኖር ብቻ
ሳይሆን ለአምላክ ሊፈጸም ስለሚገባው ሥርዓተ አምልኮ ጽንሳ,ሰ ሃሳብ ጭምር በውስጡ ይዝል፡፡

ሃይማኖት፡- ሃይማኖት – ሃይመነ ካለው የግእዜ ቃል የወጣ ሲኾን ትርጉሙም ማመን ፥ መታመን ፥ አማኝነት ፥ አመኔታ
፥ እምነት ፥ ጽኑ ተስፋ በልብ በረቂቅ ሓሳብየሚሳል ማለት ነው ፡፡ሃይማኖት ቃሉ እምነት ማለት ነው ፡፡ ሃይማኖት በአኹኑ
አነጋገር የነገረ መለኮትን ትምህርት የአምልኮትን ሥርዓት ፥ከእምነትምየተነሣ የሰውን አካኼድ ያጠቃልላል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ሃይማኖት የሚለውን ቃል በሌላ ቃለትም ተክቶ ሲያነሳ ይታያል፡፡ ለምሳሌ እምነት፤ መሠረት፤
መንገድ፤ የሚሉ ስሞችን ሃይማት የሞለውን ተክተው ተለዋጭነት አገልገሎት ላይ ውለዋል፡፡
2ኛ ቆሮ 13፤5 1ኛ ቆሮ 16፤13 ኤፌ 4፤5 ቆላ 2፤7

ሃይማኖት ከየት መጣ?

ሃይማኖት መቼ ተጀመረ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ሃይማኖተኞቹ ፍጥረታት እነማን ናቸው የሚለውን ቀድመን
ማንሳት የግድ ይለናል፡፡ በእርግጥ ፍጥረታትሁሉ ከፈጠራቸው ፈጣሩ ጋር የራሳቸው የሆነ ልዩ ግንኙነት አላቸው፡፡
ማቴ 27፤45 ዩና 1፤11 ዘጻ 14፤21 2ኛ ነገ 2፤14
ነገር ግን ፈጣሪ መኖሩን አውቀው እንያምኑ እና እንዲያመልኩ እውቀት እና ያወቁትንም እንዲፈጽሙ ሥርዓት
የተሰራላቸው ከሃያ ሁለቱ ሥነ ፍጥታት መካከል ሁለቱ ናቸው፡፡ ቅዱሳን መላዕክት እና የሰው ልጆች፡፡ስለዙህ ሃይማኖት
መቼ ተጀመረ ስንል አንደኛ ሃይማት በማን ተጀመረ ማለታችን ነው፡፡ ማለትም በሰው ወይስ በመላዕክት በዋናነት ግን
በሰው ዘንድ ሃይማት መቼ ተጀመረ የሚለውን ለማየት ነው፡፡

የሃይማኖት አጀማመር በመላዕከት

በዕለተ ዕሁድ ከተፈጠሩት ሰባት ፍጥረታት አንዱ መላዕክት ናቸው፡፡ እግዙኣብሔር በነገድ መቶ ቁጥር እጅግ
እልፍ የሆኑት መላዕክት ካለመኖር ወደመኖር አምጥቶ ከፈጠራአ,ቸው በኃላ ተሰወረባቸው፡፡ መሰወሩ አንደኛ
ከመታየት በላይ መሆኑን ላመመልከት ነው፡፡ ሁለተኛም በተሠጣቸው ዕውቀት ተመራምረው ያውቁት ዘንድ
ነው፡፡ መላዕክትም በተሠጣቸው ዕውቀት ተመራምረው ማን ፈጠረን ከየት መጣን በማለት እርስ በእረሳቸው
መጠያየቅ ጀመሩ ፡፡ ይኸውም እነርሱ የፈጠረ አምላክ እንዳለ ከማመን የመነጨ ጥያቄ ነው፡፡ዲያቢሎስ ይኼኔ
እኔ ነኝ የፈጥርኳቹህ በማለቱ መላዕክት ፈጥርህ አሳየን ቢሉት ፈጥሮ ማሳየት ባለመቻሉ በጊዛው ቅዱስ
ገብርኤል የፈጠረንን እስናውቅ ድረስ ጸንታቹህ ቁሙ በማት መላዕክን አረጋግቷቸዋል፡፡ ከዙህም በኃላ
እግዙኣብሔር በብርሃን ተገለጸላቸው ስለሆነም በሳጥናዔል እና በሀሳቡ ያመኑ ወድቃዋል ነገር ግን ፈጣ አለ
ብለው ያመኑት ክብርን ተጎናጽፈዋል፡፡

የሃይማት አጀማመር በሰው ልጆች

በሰው ልጅ ዘንድ ሃይማኖት መቼ ተጀመረ ለሚለው ጥያቄ መልስ ለማግኘት ሰው መቼ ተፈጠረ የሚለውን
ጥያቄ መመለስ ብቻ በቂ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰው ሃይማኖትን ማለትም የፈጣሪ መኖር መቀበልና ለትዕዛዝም
ተገዥ መሆን የጀመረው በተፈጠረበት ዕለት ነውና፡፡

የሃይማኖት እና የእምነት ልዩነት

ሃይማኖት-ሃይማኖት የሚለው ቃል የሚገልጸው አንድ ሰው የሚያምነው የእምነት ይዘቱ ወይም
አስተምህሮው ምንድነው የሚለውን ነው፡፡ በተጨማሪመው ሃይማነት አንድ ሰው እውነት ነው ብሎ የያዘውን
ነገር ምንነት የሚያመለክት ቃል ነው፡፡በተለዬ ሁናቴ የአምልኮ ወይም የእምነት መርህ ሲሆን አብዚኛውን ጊዛም
የሥነ ምጋር እና የመንፈሳዊ ፍልስፍና ደንቦችን በውስጡ የሚካተት ነው፡፡ ሃይማኖት ሕዜብ የሚመራበት
የግበረ ገብ የመመሪያዎች ፤የእምነት፤ የደንቦችና የመንፈሳዊ ሥርዓቶች ስብስብ ነው ፡፡
ሃይማኖት በብዘ መዜገበ ቃት የሚገለጹ በአንድ ወይም በብዘ አማዕክት ማመን ወይም ደግሞ ከሰው አቅም
በላይ ያለን አንድ ኃይል በማመን ማምለክ የሚል ነው፡፡

እምነት – እምነት ደግሞ አንድ ሰው አምነዋለሁ በሚለው ነገር ላይ ያለው መታመን ነው፡፡ እምነት አንድ ሰው
እውነት ነው ብሎ ለያዘው እና አምነዋለሁ ለሚለው ነገር ያለው ውስጣዊ መታመን ነው፡፡ በአንድ በሆነ ነገር ላይ
ያን ሙሉ አመኔታ እና መተማመን ነው፡፡እምነት ያላየነውንም ሆነ ያልዳሰስነውን ነገር ሐሳብ በልብ አመኔታ
የምንቀበልበት ኃይል ነው፡፡
በአጠቃላይ ሃይማኖት አጠቃላይነት ያለው ሲሆን አምነት ደግሞ ግላዊነት ያለው ነው፡፡ በተጨማሪም እምነት
ከሃይማኖት ጋር በአጠቃላይ ተዚማጅነት ያለውን ስያሜ ሲሆን በሃይማኖት ውስጥ እምነት የሃይማኖት
አስተምህሮ ከመረጃ ይልቅ በመንፈሳዊ የአዕምሮ ጽናት የምንቀበልበት ጠንካራ አመኔታ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *